የተለመዱ ጥያቄዎች

የሃበታም ሎተሪ ምንድነው?

ሃብታም ለኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ወይም ከኢትዮጵያ ውጭ በውጭ አገራት ለሚኖሩ ብቻ የተሰራ የኦንላይን ሎተሪ ነው፡፡ አባላት ነፃ የሃብታም አካውንት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በመቀጠልም በተዘጋጁት የዕቃ ሎተሪዎች ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ካሸነፉም ሽልማታቸው በራሳቸው ትዕዛዝና ፍላጎት በሚሠጡት የተቀባይ አድራሻ መሠረት ለቤተሰብ አባል ወይም ለጓደኛቸው መላክ ይችላሉ፡፡ ይህም ማለት፡- አሸናፊዎች ሽልማታቸውን እንደ ስጦታ አድርገው ለሚፈልጉት ሰው መስጠት ይችላሉ ማለት ነው፡፡

በክፍያ መፈጸሚያ አድራሻ እና በመላኪያ አድራሻ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

የሃብታም ሎተሪ በክፍያ መፈጸሚያ ገጽ ላይ የመላኪያ አድራሻ ማስገቢያ አማራጭ ላይኖረው ይችላል፡፡ ስለዚህ እኛ አገልግሎቱን ክፍት እስካላደረግነው ድረስ እርስዎን ምንም ሊያስጨንቀቀዎት አይገባም። ግን ምናልባት ለሌላ የስጦታ ዕቃ በሃብታም ለቀጥታ ሽያጭ ቀርቦ ከሆነ በእነዚህ ሁለት አድራሻዎች መካከል ያለውን ልዩነት መገንዘብ አለብዎት፡፡

-> የቢሊንግ አድራሻ (Billing Address) ማለት በእርስዎ ክሬዲት ወይም ዴቢት ካርድ ላይ ያለው አድራሻ ሲሆን ፤ እርስዎ በሃብታም ላይ የሎተሪ ቲኬት ሲገዙ በቀጥታ አድራሻው በጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሰዎች በተለምዶ ይህን የክሬዲት ካርዱ ላይ ያለውን አድራሻ የኦንላይን ሱቁ ክፍያ መፈጸሚያው ገጽ ላይ ይጠቀሙታል፡፡

-> የመላኪያ አድራሻ (Shipping Address) ማለት የእርስዎ የግዢ ትዕዛዝ የሚደርስበት ወይም ዕቃው የሚላክበት አድራሻ ነው፡፡ ይህ አድራሻ የግድ በኢትዮጵያ መሆን አለበት፡፡

ክፍያ ከፈጸምኩኝ በኋላ የሎተሪ ቲኬቴን ከየት ማግኘት እችላለው?

እርስዎ ክፍያውን እንደፈጸሙ በ24 ሰዓት ውስጥ በልዩ ኢ-ሜይል የሎተሪ ቁጥር ይላክልዎታል፡፡ (ይህ ኢሜይል ክፍያ መፈጸሙን ከሚያረጋግጠው ኢ-ሜይል ይለያል) በ24 ሰዓት ውስጥ ምንም ኢ-ሜይል ከሃብታም ካልደረስዎ እባክዎ የSpam እና Junk ፎልደሮችን ቼክ ያድርጉ፡፡ አሁንም ካላገኙ 24 ሰዓቱ ሲሞላ መልዕክት ይላኩልን፡፡ መልሰን የትኬት ቁጥርዎትን በኢ-ሜይል አድራሻዎ እንልካለን፡፡

ብዙ ትኬቶችን መግዛት እችላለሁኝ?

ለመልካም ዓላማ እና በእርግጥም ለመጥፎ ዓላማ እስካልሆነ ድረስ ብዙ ትኬቶችን እንዲገዙ ተፈቅዶልዎታል፡፡ ከገዙት ትኬትዎ መካከል በአንዱ ቲኬትዎ ካሸነፉ ሽልማቱ የእርስዎ ነው፡፡

የሎተሪ ቲኬቴን ለሌሎች ዙሮች መጠቀም እችላለው?

የሎተሪዎ ቁጥር ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል ቁጥር ነው። ለሌሎች ዙሮች መጠቀም አይችሉም፡፡ ቁጥርዎ ካልተመረጠ አገልግሎቱ አብቅቷል ማለት ነው። እንደገና በሌላ ዙር ሌላ አዲስ ቲኬት ገዝተው ዕድልዎን መሞከር ይችላሉ፡፡

የሎተሪውን ያለበትን ሂደት እንዴት መከታተል (ማወቅ) እችላለሁ?

የሎተሪው ሂደት 100 እንደደረሰ በሃብታም ቲቪ የዮቲዩብ ቻናል ላይ የቀጥታ ፕሮግራም ይኖረናል፡፡ ወዲያውም የአሸናፊ የመለየት ሥራው ስለሚከናወን ሂደቱን መከታተል ይችላሉ፡፡ አሸናፊው በሃብታም ድረ-ገጽ ላይ ስለሚለቀቅ ድረ-ገጹንም ቼክ ማድረግ ይችላሉ፡፡ --> HABTAM.com የቀጥታ ስርጭቱን መከታተል ሳይችሉ ቀርተው የእርስዎ የሎተሪ ቁጥር አሸናፊ ከሆነ እኛ ራሳችን ስለምናገኘዎት ምንም ሊያሳስብዎት አይገባም፡፡

ካሸነፍኩ ምን ይሆናል?

እርስዎ ከተመረጡ ወይም ማንኛውንም የሃብታም ሎተሪ ካሸነፉ ሽልማቱን የማድረሻ አድራሻውን እንዲልኩልን እናነጋግርዎታለን፡፡ የመላኪያ አድራሻው በመለያዎ ላይ በተመዘገበው የኢሜል አድራሻ ከተረጋገጠ በኋላ ለጓደኛዎ ፣ ለቤተሰብዎ ወይም ለሌላ ህጋዊ ሰው በሚኖረን በኢሜይል መልዕክት ልውውጣችን ውስጥ ለተጠቀሰው ሰው ሽልማቱን እንሰጣለን፡፡ ስለዚህ አሸናፊ ከሆኑ ኢሜልዎን ይፈትሹ እንዲሁም ስልክዎን ከአጠገብዎ አያርቁ፡፡

የሃብታም ምርጥ ነገሩ ምንድነው?

ማስተዛዘኛ የሚባል የተጨማሪ ሽልማቶች መሸለሚያ ፕሮግራም አዘጋጅተናል፡፡ ስለዚህ በዙሩ ሁኔታ ላይ በመመስረት ለሌሎች ብዙ ሰዎች ይህንን ሽልማት እንደምንሸልም ተስፋ አለን፡፡ 

በማንኛውም መንገድ ለማጭበርበር ከሞከርኩ ምን ይፈጠራል?

የውስጥ አሠራራችን ሙሉ በሙሉ ከኦንላይን ውጪ ስለሆነ እኛን ማታለያ ምንም መንገድ የለም! ነገር ግን ድንገት በማናውቀው መንገድ እኛን ለማታለል ከሞከሩና ከተያዙ መለያዎ ይታገዳል። በድጋሚ እንዳይጫወቱም ብላክ ሊስት ውስጥ ይባሉ፡፡ ቢያሸንፉም ሽልማትዎን ለሌላ አዲስ አሸናፊ ሰው እንሸልማለን!

በፈቃዳችን ያቆምናቸው አገልግሎቶች ጥያቄዎች

የሃብታም መለያ እንዲኖረኝ መክፈል ያስፈልገኛል? (የአካውንት አገልግሎትን እንዳይሠራ አድርገነዋል)

በፍጹም! የሃብታም አካውንት ሲፈጥሩ ምንም ዓይነት ክፍያ መክፈል አይጠበቅብዎትም፡፡ 100% ነጻ ነው፡፡ ክፍያ የሚከፍሉት በእያንዳንዱ ሎተሪ ላይ ሲሳተፉ ብቻ ነው፡፡

(የአካውንት አገልግሎትን እንዳይሠራ አድርገነዋል)

አካውንቴን ለሌሎች ሰዎች ሼር ማድረግ እችላለሁን? (የአካውንት አገልግሎትን እንዳይሠራ አድርገነዋል)

አይ! መለያዎን ለሌሎች ሰዎች ማጋራት አይችሉም። ያንን ካደረጉ ከእኛ የውሎችና እና ሁኔታዎች ደንብ ውጪ እየሄዱ ነው ማለት ነው። (ውሎችና ደንቦችን ይህንን ተጭነው ያንብቡ) ስለዚህ፡- ያንን ካደረጉ አካውንትዎ ይታገዳል፡፡

(የአካውንት አገልግሎትን እንዳይሠራ አድርገነዋል)

የእኔ መለያ ይፈጠራል ምን ይከሰታል? (የአካውንት አገልግሎትን እንዳይሠራ አድርገነዋል)

ለመለያዎ ተጠያቂው እርስዎ ነዎት! መለያዎ ከተጠለፈ በGoogle አካውንትዎ ወደ ሃብታም ላይ ለመግባት ይሞክሩ እና አዲሱን የሃብታምን የይለፍ ቃልዎን ይቀይሩ፡፡ አሁን ላይ እኛ ስላላስጀመርነው በሃብታም ላይ ለመግባት የይለፍ ቃል ባያስፈልግዎትም የይለፍ ቃልዎን መለወጥ ግን ይችላሉ፡፡ ወደፊት ግን ሰዎች በይለፍ ቃል እንዲገቡ መፍቀድ ከጀመርን ያስፈልግዎታል።

(የአካውንት አገልግሎትን እንዳይሠራ አድርገነዋል)